በእና/እና/ወረዳ እና በደ/ወርቅ ከተማ የሚገኙ የተፈጥሮና ሰዉ ሰራሽ የመስህብ ሃብቶች

   
    1. የተፈጥሮ የመስህብ ሀብቶች                             2. ሰዉ ሰራሽ የመስህብ ሀብቶች
ተ.ቁ የመስህብ ቦታዉ
ስም
የሚገኝበት ቀበሌ ከከተማው ያለዉ
ርቀት በኪ.ሜ
1 ሐና ዋሻ ቤተ መቅደስ እነሚ የዲጥ 19
2 መስፍን ዋሻዎች ቋሚ ጨርቅ 34
3 አራዳ ጊዎርጊስ ዋሻ ንዋየ ማርያም 25
4 አባ ፕሉፓዴር ዋሻ መጣያ 17
5 ድንጃሜ ቋጥኝ ዋሻ ፈ/ድንጃሜ 22
6 ቅባብ ዋሻ ዲያጠባ 9
7 አራራ ዋሻ(ጉራንጉር) አራራ ጠሞስ 53
8 እነነዘር ፏፏቴ መጣያ ጎረፍ 17
9 ዉርግርግ ፏፏቴ ዲያጠባ 9
10 የከረሚት ጥብቅ ደን ዲያጠባ 9
11 አራራ ፍል ዉሃ አራራ ጠሞስ 53
12 ሶማ የተፈጥሮ ድልድይ ሶማ 57
13 ጥቋሳ የተፈጥሮ ደን ፈ/ድ/ዛ/ባድማ(ጥቋሳ) 25
14 የተክለ ሃይማኖት ዋሻ ፈ/ድ/ዛ/ባድማ(ጥቋሳ) 25
ተ.ቁ የመስህብ ቦታዉ
ስም
የሚገኝበት ቀበሌ ከከተማው ያለዉ
ርቀት በኪ.ሜ
1 የፃዲቁ ዮሃንሰ ፍርስራሽ ግንብ ደ/ወርቅ
2 ደጃች ዮሃንሰ ፍርስራሽ ግንብ ቋሚ ጨርቅ 34
3 ፀሃይ ነገዳ ፍርስራሽ ግንብ ገደብ 26
4 ጀር ቅዱስ ገብርዔል ዋሻ ዱገደል አጋምና 3
5 ሶማ የጠጅ መበጥበጫ ጋን ሶማ 57
6 የአያልፉሽ ተራራ አገዉ ካብ ዱገደል አጋምና 4
7 የደ/ወርቅ ማርያም ቤተክርስትያን ደ/ወርቅ
8 የደ/ወርቅ ማርያም ዘመናዊ ሙዚየም ደ/ወርቅ
9 ጀር ቅዱስ ገብርዔል አንድነት ገዳም ዱገደል አጋምና 3
10 ደብረዘይት ቅዱስ ሚካዔል ቤተክርስትያን እነሚ ደብረ ዘይት 20
11 ድንጃሜ ማርያም ገዳም ፈ/ድ/ዛ/ባድማ 25
12 የፈላሴ ጥብቅ ደን ደጅ አጋምና 3
13 መካነ-ህይወት ደብረ ቅዱሳን የጎዲት አቦ ቤተክርስትያን እነዳራ መጣያ 25
14 የተክለ ሃይማኖት ዋሻ ፈ/ድ/ዛ/ባድማ(ጥቋሳ) 18
14 አምባላይ ጊዎርጊስ ሰዉ ሰራሽ ደንና ቤተክርስትያን ባድማ 15

ተክለ ኃይማኖት ዋሻ (ፈለገ ዛቸና)

የተክለኃይማኖት ዋሻ በነ አፄ ዮኃንስ አፄ በዕደ ማሪያም እና አፄ ሱስንዮስ ዘመን ቀኝ አዝማች መስፍን እና ቀኝ አዝማች በላይ ዘለቀ ሸፍተዉ እንደ መሸሸጊያ የተጠቀሙበት እና የአካባቢዉ ህብረተሰብ በክፉ ቀን ዉድ የሆኑ የቤተክርስትያን እቃዎችን፤የብራና መጽሓፍትን እና ቤተሰቡን በመያዝ ቀን የወጣበት ፤ በአሁኑ ሰዓት ደግሞ ጠበሉ አሁን ካለበት አካባቢ የነበረዉ ተክለኃይማኖት በራሱ ፈቃድ ከነበረበት በመነሳት በዋሻዉ አልፎ ዛቸናገብርዔል በመግባቱ በተ/ኃይማኖት ስም የተሰየመዉ ጠበል የአካባቢዉን ህዝብ ከተለያዩ በሽታዎች በመፈወስ ይታዎቃል፡፡ በጠበሉ ሰዎች ሊጠመቁ ሲገቡ ቀስተዳመና ይታያቸዋል፡፡ በጠበሉ የተፈወሱ እና በየጊዜዉ በስለት የተለያዩ ታምራት የተደረገላቸዉ ሰዎች በርካታ ገቢ ለጠበሉ ያስገባሉ፡፡ አባቶች እንደሚሉት ደግ አባቶች በዋሻዉ ገብተዉ ቤተክርስትያን ይወጡ ነበር፡፡ በዉስጡም ዛፎች እና ምንጭ እንዳለ ይናገራሉ፡፡


ጥቋሳ የተፈጥሮ ደን (አቦ ገዳም)

በጥቋሳ ሚካዔል የሚገኝ የተፈጥሮ ደን ሲሆን በ10 ሄክታር መሬት ላይ የተከበረ ጥቅጥቅ የተፈጥሮ ደን ነዉ፡፡ የደን ስፍራዉ በሁለት ጥበቃ ሰራተኞች የሚጠበቅ ሲሆን አንዱን የዛቸና ገብርዔል ህዝብ በየወሩ 300 ብር እየከፈለ የሚያስጠብቀዉ እና ሌላዉን ደግሞ የጥቋሳ ሚካዔል ህዝብ በየወሩ 300 ብር እየከፈለ የሚያስጠብቀዉ ዉብ የተፈጥሮ ደን ነዉ፡፡ -በደኑ ዉስጥ በርካታ የዱር እንስሳት የሚገኙ ሲሆን ለአብነት ጅብ፣ቀበሮ፣ዝንጀሮ፣ሚዳቋ፣ድኩላና የተለያዩ የወፍ ዝርያዎች ይገኛሉ፡፡


አራራ ባዕታ

አራራ ባዕታ ገዳም በእናርጅ እናዉጋ ወረዳ በምስራቅ አቅጣጫ 28 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኝ ገዳም ናት፡፡ ገዳሟን በ 14 ኛዉ ክፍለ ዘመን በአራራ ቀበሌ የሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎች ለክርስትና እምነት ማምለኪያ በማለት እንደመሰረቷት የአካባዉ ነዋሪ የሆኑት ግራ ጌታ ካሳ ጓዱ ይናገራሉ፡፡እኒህ አባት እንደሚሉት ገዳሟ ስትመሰረት የአካባቢዉ ህብረተሰብ በዙርያዋ ቤት በመስራት የሚኖሩ ሲሆን ህብረተሰቡም ቅዱሳን ሌሊት ኪዳን ሲያደርሱ ይሰሟቸዉ እንደነበር ይናገራሉ፡፡ ከጊዜ በኋላ ህዝቡ እየበዛ በእለት ከእለት እንቅስቃሴዉ ለገዳሟ ቅዱሳን ስላልተመቻቸዉ ሌሊት የህብረተሰቡን ስም መጥራት ጀመሩ፡፡ስሙ የተጠራዉ ሰዉ ደግሞ በጥቂት ቀን ዉስጥ ይሞታል፡፡ በዚህ መቅዘፍት የተነሳ ህዝቡ ተሰባስቦ በመወያየት ህብረተሰቡ ከቤተክርስትያኑ እንዲርቅ ተስማሙ፡፡በዚህ ስምምነት መሰረት ህብረተሰቡ አሁን በተለምዶ ጨጨር እና መስተዎት እየተባለ ከሚጠራዉ ጎጥ ቤት በመስራት መስታዎት ከሚባለዉ ጎጥ የሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍል ጊወርጊስ ታቦትን በመትከል እና በመዘከር እንዲሁም በጨጨር ጎጥ የሚኖሩት ደግሞ ባዕታን ታህሳስ 3 እያከበሩ ሰዎች ሲታመሙ ደግሞ አባቶች ተሰባስበዉ በባዕታ ለ7ቀን ፀሎት ሲያደርጉላቸዉ ይፈወሳሉ፡፡አፄ በእደማርያም ከ1468-1478ዓ.ም ግራኝ መሀመድን በተዋጉበት ጊዜ ሰራዊታቸዉን በአራራ ባዕታ አካባቢ በማስፈር ባዕታ ማርያምን በመማፀን ድል ማድረግ ችለዋል፡፡በአሁኑ ሰዓት በገዳሟ ዉስጥ 3 (ሶስት)ወንድ.እና 2 (ሁለት)ሴት በድምሩ አምስት (5) መነኮሳት የሚኖሩ ሲሆን የቀበሌዉ ህዝብ በምፅዋት መልክ በሚሰጣቸዉ እና ከገዳሟ በተሰጣቸዉ መሬት በመጠቀም ይኖራሉ፡፡ገዳሟ ሰፊ የተፈጥሮ ደን በግቢዋ ያላት ሲሆን በደኑ ዉስጥ በዓይን የማይታዩ አልፎ አልፎ የሚከሰቱ ቅዱሳን አባቶች፣ አእዋፍት እና ብርቅየ የዱር እንስሳት ይገኙባታል፡፡


የደብረ ወርቅ ማርያም ገዳም ቤተክርስትያን

ገዳሟ በደ/ወርቅ ከተማ ከከተማዉ በስተ ምስራቅ አቅጣጫ በተለምዶ አባ ሰላማ እየተባለ ከሚጠራዉ አካባቢ ከፍ ብሎ ከሚታየዉ ቦታ ላይ ያለች ሲሆን ፡- ገዳሟ በ351 ዓ.ም በአስፍሐ ወአፅብሃ ተመሰረተች፡፡ከዚህም ጊዜ ጀምሮ መስዋዕተ ኦሪት ይሰዋባት እንደነበር አባቶች ያስረዳሉ፡፡ ገዳሟ ከተሰራች ከ506 ዓመት በኋላ በ857 ዓ.ም በዮዲት ጉዲት ተቃጠለች፡፡ከዚህም በኋላ በ1372 ዓ.ም በቀዳማዊ ዳዊት በድጋሜ ተሰርታ አገልግሎት እየሰጠች ከቆየች በኋላ በ1533 ዓ.ም በአፄ ገላዉዲዎስ እንደገና ለአሁኑ ትዉልድ የደረሰዉ የመቅደሷ ህንፃ በኖራ ታደሰ፡፡ በአጠቃላይ ገዳሟ ከ250 እስከ 351 ዓ.ም በኦሪት ከዚያም እስከ አሁን ድረስ ክርስትናን ተቀብላ አገልግሎት እየሰጠች ትገኛለች፡፡ በውስጧ በርካታ ቅርሶች ያላት ሲሆን ለአብነት፡-ወንጌላዊ ቅዱስ ሉቋስ የሳላት ወይኑት የምትባል የእመቤታችን ስዕል፡፡ ከወርቅና ከአልማዝ የተሰራ የአፄ ዮሃንስ ዘውድና የነገስታት ልዩ ልዩ ዘዉዶች፡፡ ከወርቅና ከብር የተሰሩ የእጅና የመፆር መስቀሎች፡፡ የአባ ሰርፀ ጴጥሮስ ቆብ፣ መቋምያ፣ የብረት ልብስና መስቀል፡፡ የአፄ ቴዎድሮስ ባለቤት የነበሩት ወ/ሮ አበሻ ያበረከቱት የተለያየ የብርና የወርቅ ጉብጉባት ካባዎች፡፡ መስዋዕተ ኦሪት የሚሰዋበት እንደ መቅረዝ፣ ሰንና ብርት ያሉ ቅርሶች፣ የተለያዩ ጥንታዊ የብራና ጽሁፎች ወዘተ፡፡ ከነዚህም ቅርሶች መካከል ከየዓይነቱ በደ/ወርቅ ማርያም ዘመናዊ ሙዚየም በማስገባት ለማንኛዉም የሃገር ዉስጥና የሃገር ውጭ ቱሪስቶች ለጉብኝት አመች በማድረግ ለጎብኝዎች የመዝናኛና የጥናትና ምርምር አገልግሎት በመስጠት ለወረዳዉ የቱሪስት ፣ ለቤተ ክርስትያኗ ደግሞ የገቢ ምንጮች ናቸዉ፡፡ ገዳሟ የገቢ ማስገኛ የእርሻ መሬት ያላት ሲሆን በተጨማሪም ከአማኙ ህብረተሰብ የሚገኘዉ የስለት ገቢ፣ አትክልትና እርባታም የገቢ ምንጮችዋ ናቸዉ፡፡


የደጃች ዮኃንስ ፍርስራሽ ግንብ

የ 80 አመት የእድሜ ባለፀጋ የሆኑት የቀበሌዉ ነዋሪ አቶ ማናየ ሰዋገኝ በሰጡን መረጃ መሰረት ግንቡ የተሰራዉ በ16ኛዉ መቶ ክፍለ ዘመን በጎንደር የህንፃ ጥበብ በአመድ፣ በድንጋይ፣ በኖራና በጥናዉግ እንደሆነና የተሰራበት ምክንት ደግሞ ደጃች ዮሃንስ የአፄ ፋሲልን ልጅ ኢሌኒን አግብቶ በጎንደር ኑሮ መስርቶ እቴርጊስ(እህተ ማርያም) ወልደ ጊዎርጊስ የሚባሉ ልጆችን እንደወለደና እህተ ማርያም ደግሞ ፋሲልና ዳግማዊ ዮሃንስን ዳግማዊ ዮሃንስ ደግሞ ፍታራይ መስፍንን የወለዱ መሆኑን የዘር ሃረጋቸዉን እየዘረዘሩ ነግረዉናል፡፡ ከዚህ በኋላም ደጃች ዮሀንስ ከኢሌኒ ጋር አልስማማ በማለት ወደ ገንገርታ በመምጣት ሚስት አግብቶ እየኖረ እያለ ኢሌኒ ሰምታ ከኔ የተሻለች ካገባህ ይሁን ፈቃዴ ነዉ የመሳመሳ ከሆነ ደግሞ ልወጋህ ቀጠሮ ይዣለሁ በማለት መልክተኛ ትልክበታለች ከዚያም ደጃች ዮሃንስ ከገንገርታ ወደ እናርጅና እናዉጋ ወረዳ ቋሚጨርቅ ቀበሌ በመሰደድ ከኢሌኒ ጋር ለመዋጋት የሚያስችል ዝግጅት እንዳደረገና ህንፃዉንም እንዳሰራዉ ነግረዉናል፡፡


የጠጅ መበጥበጫ ጋን

በእናርጅና እናዉጋ ወረዳ ከደ/ወርቅ ከተማ በ51 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኝ ሲሆን የቀበሌዉ ነዋሪ እና የኃይማኖት አባት የሆኑት ቄስ ታደለ እንዳሉን ፡-የጠጅ መበጥበጫ ጋኑንና የዉኃ ማጠራቀሚያዉን ያሰራዉ ደጃች ብሩ እደነበርና ደጃች በላይም በ1933ዓ.ም ከደቡብ ወሎ ወንድሙን እጅጉ ዘለቀንና ባልደረባዉን ሽፈራዉ ገርባዉን በመያዝ ስትራቴጅክ ቦታ በመምረጥ ሶማ ደጋ በመዉጣት የዉሃ ማጠራቀሚያዉንና የጠጅ መጣያዉን ጋን የተጠቀሙበት መሆኑን ነግረዉናል፡፡


የጀር ቅዱስ ገብርኤል ዋሻ

የጀር ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ቤተ- ክርስቲያን ከደ/ወርቅ ከተማ በ 3 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኝ ሲሆን በ16ኛው ክፍለ-ዘመን በነገሱት አፄ ገላውዲዮስ ዘመነ- መንግስት በ1530ዎቹ የደ/ወርቅ መምህር በነበሩት በአባ ሠበነ-ጴጥሮስ መንፈሳዊ አባት አማካኝነት እንደተተከለ መጽሀፍትና የኃይማኖት አባቶች ይናገራሉ፡፡ የጀር ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ቤተ- ክርስቲያን ጥንታዊ መጠሪያ ፈላሴ ይባላል፡፡ ፈላሴ ከባህር ጠለል በላይ ከ2700 እስከ 2900 ከፍታ ባለው በ438.5 ሄ/ር ጥብቅ የመንግስት ደን ላይ የሚገኝና ግርማ ሞገስ ተላብሶ የደኖች ቁንጮ የብርቅየ የዱር እንስሳት መኖሪያ በሆነው ደን የተራራው ቁንጮ በመሆን በአራቱም አቅጣጫ በርቀት የሚታየው ፈላሴ የቦታውን ስያሜ ያገኘውም እንደ አባቶች ገለፃ አባ ሠበነ-ጴጥሮስ በደ/ወርቅ በእመቤታችን ስም ቤ/ክርስቲያን መተከሉን በማገናዘብ በቅድስት ድንግል ማርያም በስዕለ-አድኖ በግራና ቀኝ የቅዱስ ሚካኤልና የቅዱስ ገብርኤል ስዕሎች እንደማይለያዩ ሁሉ በዚህ መልክ የሁለቱም ቤተክርስትያን የመተከላቸዉ ሃሳብ ለአፄ ገላዉዲዎስ ሲነገራቸዉ አፄ ገላዉዲዎስም በተለይ ለቅዱስ ገብርኤል መትከያ የተባለዉ ቦታ ከሌላ አካባቢ ለሚመጡ መናንያን ወደ ቅድስት ሀገር ደ/ወርቅ በአንድነት ሲመጡ የፈላስያን ማረፍያ ሆኖ የተጠመቁ አመክሮ የሚሰጡበት ፤ያልተጠመቁና በአምልኮ ጣኦት የቆዩ ዝቅ ብሎ ከሚገኘዉ እስካሁን ጨዳ ተብሎ በሚጠራዉ ቦታ ቄደር ተጠምቀዉ ወንዙን ተሻግረዉ ወደ ዋናዉ ቤተ-ማህበር እንዲገቡ ያገለግል ስለነበር ፈላስያን ያድሩበት በነበረዉ አካባቢ ቤተ-ክርስቲያን ተሰራ፡፡ ቦታዉም ፈላሴ ተብሎ እንደተጠራ ይነገራል፡፡ የጀር ቅ/ገብርኤል ገዳም ቤተ-ክርስቲያን ስያሜዉን ያገኘዉ በሁለት መንገድ ነዉ፡- አንደኛዉ ወደ አካባቢዉ ከሩቅ የሚመጡ መናንያን ለሱባኤ የሚመጡ አባቶች የሚመገቡት እንጆር የተባለ ፍራፍሬ በብዛት የሚገኝበት ስለነበር መካነ- እንጆር ከሚለዉ ጆር እንደተባለ ሲነገር፡፡ ሁለተኛዉ፡- በ17ኛዉ ክፍለ ዘመን በአዔ ሱስንዮስ ዘመነ-መንግስት ካቶሊኮች ወደ ሃገራችን ገብተዉ ሊቃዉንትንና ቤተ-ክርስቲያንን ማሳደድ በጀመሩ ጊዜ ለእዉነተኛዋ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ኃይማኖታቸዉ ምስክርነት ሰጥተዉ በደ/ወርቅ የተሾሙት መምህር አርከ ድንግል ከሄዱበት ሰማዕትነት ሸሽተዉ ከእስራት ለማምለጥ ተመልሰዉ ጆር ላይ ሲደበቁ የበቁ ደግ አባት ከጫካዉ ወጥተዉ አንተ ማነህ  ወደየትስ እንጀር እንጀር ትላለህ አሏቸዉ እሳቸዉም እኔ አርከ ድንግል ነኝ ሲሏቸዉ ምን አርከ ድንግል አርከ ሰይጣን እንጂ ለእዉነተኛዋ የኦርቶዶስ ኃይማኖት መስክረህ መስዋዕት በመሆን ፈንታ ክብር ሰማዕትነት የሽሸህ ብለዉ ተናግረዋል ፡፡ መምህር አርከ-ድንግልም ሳይመለሱ በዚያዉ ዋልድባ ገብተዉ መንነዋል፡፡ የጀር ቅ/ገብርኤል ገዳም ሌላው ታሪካዊ አሻራ አጼ ቴዎድሮስ/ የቋራው ካሳ /ከራስ አሊ ጋር ተጣልተው በተንቀሳቀሱ ወቅት ከቦታው አቀማመጥና ከፍታ የተነሳ በዚሁ ተራራ ላይ ለ3ወር ድንኳናቸውን ተክለው የአካባቢዋን የጎጃም ተወላጅ ወ/ሮ አበሻን አግብተው ተቀምጠዋል ፡፡ በተጨማሪም ደጃች ብሩ ጎሹን ሶማ ላይ ድል ለማድረግ ቋሚ ጨርቅ ላይ እንደተቀመጡ የታሪክ መጽሀፍት ያስረዳሉ፡፡ በመጨረሻም ወደ ሀገራቸው ሲመለሱ ንጉሰ-ነገስት ከተባልኩ በማለት ተስለው በመሄዳቸውና ስለታቸውም ስለደረሰላቸው ለጀር ቅ/ገብርኤል የላኳቸው ልዩ ልዩ ቅርሶች ክፉ ቀን በተባለው በርካታ አብያተ- ክርስትያናት ሲቃጠሉ አብሮ እንደተቃጠለ ሲነገር በደ/ወርቅ ማርያም ገዳም ያበረከቱት የባለቤታቸው የወ/ሮ ሀበሻ የብር ጉብጉባት ካባ አሁንም በደ/ወርቅ ሙዚየም በክብር ይገኛል፡፡


አራዳ ጊዎርጊስ ዋሻ

በነዋየ ማርያም ቀበሌ የሚገኘዉና አባቶች ከጠላት የቤተክርስትያን ንዋየ ቅዱሳትንና ቤተሰቦቻቸዉን ከክፉ ቀን ያወጡበት እንደሆነና ጥልቀቱ የማይታወቅ ሰፊ እና ረጅም ዋሻ ሲሆን በርካታ ህሙማንን እየፈወሰ ያለ ጠበልና የማይታወቁ ጽላቶችን የያዘ እንደሆነ አባቶች ምስክርነት ይሰጣሉ